loading
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ አለፈ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ አለፈ፡፡ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰአታት የኮቪድ 19 ስርጭት መረጃ ባሳወቀበት ወቅት እንደገለጸዉ፤ ባለፈት 24 ሰኣታት ዉስጥ 20 ሰዎች በኮቪድ 19 ህወታቸዉን አጥተዋል፡፡ የህም ባጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 3 ሺህ 9 መቶ 96 ደርሷል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺህ 71 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 432 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 መቶ 66 ሺህ 2 መቶ 64 ደርሷል። በሌላ በኩል 700 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 2 መቶ 19 ሺህ 566 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። 1 ሚሊዮን 460 ሺህ ሰዎች በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት መከተባቸዉ የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *