loading
በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 ደረሰ
በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።ሚኒስትሯ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ943 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን በፌስ ቡክ ገጻቸው የገለጹ ሲሆን፤በዚህም አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል፡፡ቫይረሱ የተገኘበት የ45 አመት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው መሆኑንም ነው ዶክተር ሊያ ያስታወቁት።ግለሰቡ ከእንግሊዝ የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ነው ተብሏል።እስካሁን በኢትዮጵያ 14 ሺህ 5 መቶ 88 ሰዎች ላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸዉ ሲሆን ባጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 124 ደርሷል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ 50 ዎቹ ሲያገግሙ 69 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ህክምና ውስጥ መሆናቸዉም ታዉቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *