በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነቱ ተመልሷል
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነቱ ተመልሷል
የሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንት ተካሂደዋል፤ ቀን 9፡30 በለንደን ደርቢ ዌስት ሃም በኦሎምፒክ ስታዲየም አርሰናልን አስተናግዶ በራይስ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ረትቷል፡፡
ምሽት 12፡00 ላይ ደግሞ በተመሳሳይ ሰዓት የተለያዩ ጨዋታዎች ተደርገዋል፤ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ወደ አሜክስ አቅንቶ ብራይተንን በመሀመድ ሳላህ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል 1 ለ 0 አሸንፎ ተመለሷል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች በርንሊ 2 ለ 1 ፉልሃም፣ ካርዶፍ ሲቲ 0 ለ 0 ሀደርስፊልድ ታውን፣ ክሪስታል ፓላስ 1 ለ 2 ዋትፎርድ፣ ሌስተር ሲቲ 1 ለ 2 ሳውዛምፕተን፡፡
በምሽት ሌላ ጨዋታ ደግሞ ቼልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ ኒውካስትልን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ረትቷል፡፡ ለሰማያዊዎቹ ፔድሮና ዊሊያን ሲያስቆጥሩ ክላርክ ለማግፒሶች በባዶ ከመሸነፍ ያዳነች ግብ ከመረብ አገናኝቷል፡፡
ዛሬ ደግሞ አመሻሽ 11፡15 ላይ ኢቨርተን በጉዲሰን ፓርክ ከበርንማውዝ ጋር ሲጫወቱ በዊምብሌ የሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ በቶተንሃም ሆትስፐር እና ማንችስተር ዩናይትድ መካከል ምሽት 1፡30 ይከናወናል፡፡ የጨዋታው ውጤት ለሁለቱም ቡድኖች የሚያስፈልግ ሲሆን ማንችስተር የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን ከአርሰናል ጋር ያስተካክላል በአንፃሩ ድል ለስፐርስ የሚሆን ከሆነ ደግሞ ሲቲ እስኪጫወት ድረስ ደረጃው ወደ ሁለተኛ ከፍ ለማድረግ ይጠቀምበታል፡፡
ሠኞ ምሽት 5፡00 ማንችስተር ሲቲ ኢቲሃድ ላይ ወልቭስን ያስተናግዳል፡፡
ሊጉን ሊቨርፑል በ57 ነጥብ ይመራል፤ ማ.ሲቲ ደግሞ በ50 ይከተላል፤ ቶተንሃም በ48 እንዲሁም ቼልሲ በ47 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡