በኮቪድ 19 ተይዘው በሆስፒታሉ ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው ወጡ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17፣ 2012 በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማዕከል የኮቪድ 19 ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው መዉጣታቸዉን ሆስፒታሉ አስታዉቋል ፡፡በኮቪድ 19 ፓዘቲቭ ሆነው ወደ ሆስፒታሉ የገቡት በአጠቃላይ 178 ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ ዙር 44 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን በሁለቱ ዙር አጠቃላይ 81 ሰዎች አገግመው ወጥተዋል ።
በሆስፒታሉ የኮቪድ 19 ቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ሰዎች 205 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 144 ሰዎች ነጻ ተብለው ወደ ቤታቸው ሄደዋል፡፡
በኮቪድ 19 ህክምቸውን አጠናቀው የወጡ ታካሚዎች እንደተናገሩት የጤና ባለሞያዎች ምክር መስማትና ከመደንገጥ መጠንቀቅ አዋጭ መንገድ ነዉ፡፡አንዳንድ ሰዎች ቢይዘኝም አይገለኝም በሚለው አስተሳሳብ እንዳይዘናጉና ለኛ ሳይሆን ለቤተሰቦቻችን ማሰብ አለብን ብለዋል፡፡ በሆስፒታሉ ለሚገኙ ጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በተለይም ለህጻናት፣ ለአረጋውያን እናቶችና አባቶች ማሰብ ይገባናል ብለዋል፡፡
ምንጭ፤-የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፌስቡክ ገጽ