loading
በኮንጎ በኢቦላ በሽታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ180 መብለጡ እየተነገረ ነው

በኮንጎ በኢቦላ በሽታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ180 መብለጡ እየተነገረ ነው

አርትስ 27/02/2011

 

ውጥረት በሰፈነባትና የሰሜን ምስራቅ ኮንጎ ግዛት በሆነችው ሰሜናዊ ኩቩ ውስጥ እንደአዲስ በተቀሰቀሰው ኢቦላ በሽታ በርካቶች መጠቃታቸው እየተነገረ ነው።

እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ ውስጥ በኢቦላ በሽታ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም ከ180 መብለጡን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ኤኤፍፒ እንደዘገበው ኮንጎ ውስጥ በኢቦላ በሽታው እንደተያዙ የተጠረጠሩ 298 ሰዎች የተገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 263 ሰዎች በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል። 35 ሰዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተብሏል።

የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት እንደሚናገሩት አዲስ በተቀሰቀሰው ኢቦላ የመጀመሪያ ተጠቂዎች አንዲት አራስ እናትና ጨቅላ ልጇ ናቸው።

ሁለቱም በሽታውን አንዳያስተላልፉ ለብቻቸው በተዘጋጀላቸው ማቆያ ስፍራ የህክምና አርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *