loading
በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከዩ ኤን የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነው በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና የሚሰጠው፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ስልጠናው በምርጫው ላይ በተለያዩ ዘርፎች የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን አቅም ለማሳደግ አንደሚረዳ ተናግረዋል።

ለበጎ ፈቃደኞቹ ክፍተት ባለበት ቦታዎች ላይ በተለይ በአይቲ፣ በስነዜጋ ትምህርት እና በፆታ እኩልነት ዙርያ ስልጠናው መሰጠቱ ማህበረሰቡን ለማገልገል ብቁ እንደሚያደርጋቸውም ገልጸዋል። በተጨማሪም ቦርዱ የዘንድሮውን 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ የተለየ ለማድረግ እና ሁሉም ዜጋ በማንነቱ ሳይገለል የእያንዳንዱ ሰው ድምፅ ትርጉም እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በቀጣይም የእጩዎች ምዝገባ እንደሚጀመር እና የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እንደሚካሄድ የገለጹት ወ/ት ብርቱካን፣ የምርጫ ታዛቢዎችን ገለልተኝነት የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራም አመልክተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *