loading
በዘንድሮው የአባቶች ቀን ለጋሞ አባቶች እውቅና ሊሰጥ ነው

አርትስ 05/03/2011

እዉቅናዉን  እሰጣለሁ ያለው ደግሞ ዱም ሚዲያ ኮሙኒኬሽን ነዉ፡፡

አዘጋጆቹ  በዚህ ዓመት ስለሚከበረው 10ኛው የአባቶች ቀን አስመልክቶ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነዉ የጋሞ አባቶችን እዉቅና ሊሰጡ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ወጣት ቴዎድሮስ አርጋው እንደተናገረው ቀኑን በዘጠኙም ክልሎች በመዘዋወር እና አርዓያ ለሆኑ አባቶች እውቅና በመስጠት እስከ ግንቦት 15 ቀን ይካሄዳል ብሏል፡፡

እንደ አዘጋጆቹ ገለፃ የእውቅና ስነስረዓቱ የሚጀምረው የፊታችን ቅዳሜ በአርባ ምንጭ ከተማ ጦርን በሳር ለመለሱ የጋሞ አባቶች እውቅናን በመስጠት ነው፡፡

በመሰናዶው አባቶችን እግር የማጠብ ፣የፎቶ አውደርዕይ፣ የአባቶች ቤተሰባዊ እና ማህበራዊ ሚና ላይ የሚያተኩር የፓናል ውይይት እና ሌሎችም ዝግጅቶች እንደሚካሄዱ ሰምተናል፡፡

በቀጣይ አመትም ቀኑን በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ለማክበር በአስመራ ከተማ ለማካሄድ ሂደት ላይ ነው ያሉት አዘጋጆቹ፤ አቅመደካማ ለሆኑ እና ጧሪ የሌላቸው አባቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ከበጎ እድራጎት ድርጅቶች ጋርም በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ሚዲያ ኮሙዩኒኬሽኑ ከ2003 ጀምሮ የአባቶችን ቀን በኢትዮጵያ እያከበረ ነዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *