loading
በዛሬው ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የህፃናት ማቆያ አስመረቀ

በዛሬው ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የህፃናት ማቆያ አስመረቀ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስትር  ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ በምረቃ ሥነ ሥርዓት ወቅት እንደተናገሩት፤ የህፃናት ማቆያው አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰሩ ወላጆች በተለይ ሴት ሰራተኞች ከወሊድ በኋላ ወደ ሥራ ገበታቸው ሲመለሱ ልጆቻቸውን በሥራ ቦታቸው ጡት ማጥባትና በቅርበት ተከታትለው አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ እንዲችሉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት መሆኑን ገልፀዋል።
በማቆያው ተጠቃሚ የሚሆኑ እድሜያቸው ከስድስት ወር እስከ አራት ዓመት የሆኑ ሕፃናት እንደሆኑም ታውቋል፡፡
በሚ/ር መ/ቤቱ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማሰራጫ ድርጅት ከ64 ሺ ብር በላይ የሚገመት ለህፃናት ማቆያው የውጪ መጫወቻዎችን ድጋፍ ያደረገ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከኢትዮጵያ ሴቶች ጤና ማህበር እና አጋርነት ለለውጥ ከተባለ የልማት አጋር ድርጅቶች ለማቆያው ምስረታ አስፈላጊ ግብዓት ለሟሟላት በግምት ብር 300 ሺ የሚጠጋ ድጋፍ ያደረጉ መሆኑ ታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *