loading
በድሬዳዋ ግጭት በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 54 ግለሰቦች ክሳቸው ተቋርጦ ሊለቀቁ ነው

አሁን በደረሰን ዜና በድሬዳዋ ከነበረው ሁከትና ግጭት በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 54 ተጠርጣሪዎች ከህብረተሰቡ ጋር ከሚካሄድ ውይይት ጋር ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ሊለቀቁ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ከሚለቀቁት ተጠርጣሪዎች ጋር ውይይት ይካሄዳል።

በትናንትናው ዕለት  32 ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ  ምርመራቸው ተቋርጦ ከእስር የተፈቱ መሆኑ ይታወሳል።

በቀጣይ ቀናትም እየተጣሩ ያሉ የምርመራ ስራዎች በማጠናቀቅ የህግ ተጠያቂዎችን በህግ እንዲጠየቁ የማድረግና ንፁሀንን ደሞ ከእስር የመፍታት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቋል። :

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *