loading
በጊኒ ምርጫ ማግስት በተቀሰቀሰ ግጭት አስር ሰዎቸ መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 በጊኒ ምርጫ ማግስት በተቀሰቀሰ ግጭት አስር ሰዎቸ መገደላቸው ተሰማ:: የአፍሪካ ህብረትና የምእራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ ሂደቱ ሰላማዊ ነበር ብለው :: የመሰከሩለት የጊኒ ምርጫ ውጤቱ ገና በይፋ ሳይገለፅ ብጥብጥ አስከትሏል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው የተቃዋሚ መሪው ሴሎ ዲያሎ ገና ድምፅ ቆጠራው ሳይጠናቀቅ አሸንፌያለሁ ብለው ለደጋፊዎቻቸው ከተናገሩ ከቀናት በኋላ ጊዜያዊ ውጤቱ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ እየመሩ መሆኑን ያሳያል በመባሉ ነው፡፡

ይህን ዜና ተከትሎ የዲያሎ ደጋፊዎች ለተቃውሞ አደባባይ በወጡበት ወቅት ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው አስር ያህል ሰዎች ተገድለዋል፡፡ የጊኒ የደህንነት ሚኒስትር የተፈጠረውን ሁኔታ አስመልተው በሰጡት መግለጫ ሰዎች መጎዳታቸውን አምነዋል፡፡ የዲያሎ ደጋፊዎች በዋና ከተማዋ ኮናክሪ አዋሳኝ ከተሞች ጎማዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን ጎዳና ላይ በማቃጠል መንገዶችን ሲዘጉ ተስተውለዋል፡፡

በመጨረሻም ፖሊስ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡትን ሰዎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ከተሰባሰቡበት ስፍራ በትኗቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኮንዴ በማህበራዊ ድረ ገፅ ባስተላለፉት መልእክት የምርጫው ውጤት ተጠቃሎ ይፋ እስኪሆን ድረስ ፖለቲከኞችም ደጋፊዎችም እንዲታገሱ ጠይቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *