loading
በጦላይ ተሃድሶ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች ወደየቤታቸው ተመለሱ

በአዲስ አበባ ከተማ ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 1ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ወደየቤታቸው መመለሳቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

የፖሊስ ኮሚሽነሩ እንደተናገሩት ከወጣቶቹ ጋር የጋራ ውይይት ከተደረገ በኋላ ወደአዲስ አበባ ተመልሰው ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ተደርጓል።

ወጣቶቹ በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ቆይታቸው ራስን ከወንጀል የማራቅ እና ተያያዠ ለአንድ ወር ስልጠናዎችን መውሰዳቸውን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡

ወጣቶቹ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወስ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *