ቤጂንግ የኪም እና የፑቲን ውይይት ይበል የሚያሰኝ ነው አለች፡፡
ቤጂንግ የኪም እና የፑቲን ውይይት ይበል የሚያሰኝ ነው አለች፡፡
ቻይና ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን የሚያደርጉት ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከሩም በሻገር በኮሪያ ልሳነ ምድር መረጋጋት እንዲፈጠር አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብላለች፡፡
ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጀንግ ሹዋንግ በሰጡት መግለጫ ቻይና እና ሩሲያ በቀጠናው ያለውን ውጥት ለማርገብ ሁነኛ መፍትሄ ማምጣት ይቻላሉ ብለዋል፡፡
ከሁለቱ መሪዎች ስብሰባ ብዙ መልካም ነገሮችን እንጠብቃለን ያሉት ቃል አቀባዩ አካባቢውን ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ ስጋት ነፃ ስለማድረግ የሚደረጉ ድርድሮች እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ምኞታችን ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የመጀመሪያ በሆነው የሩሲያ ጉብኝታቸው ከፑቲን ጋር በኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
መንገሻ ዓለሙ