loading
ቱኒዚያ በሰራተኞች አመፅ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች

አርትስ 14/03/2011

የቱኒዚያ የሰራተኞች ማህበር በደመወዝ ጥያቄ ከመንግስት ጋር ያደረገው ድርድር ባለመሳካቱ ምክንያት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡

ፕሬስ ቴሌቪዥን እንደዘገበው የሰራተኛ ማህበሩ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ በወር ቢያንስ ከ15 እስከ 30 ዩሮ የደመወዝ ጭማሪ እንዲያደርግ መንግስትን ጠይቋል፡፡

በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ከ3 ሺህ በላይ በሆኑ ሰልፈኞች የተጀመረው የሰራተኞቹ አመፅ አሁን ላይ  ሀገር አቀፍ ይዘትን ተላብሶ በመላ ሀገሪቱ ተስፋፍቷል ነው የተባለው፡፡

 

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ  ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተውጣጡት ሰልፈኞች ከፈረንጆቹ 2013 ወዲህ ቁጥራቸው ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡

ቱኒዚያ በአንድ በኩል የሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ በሌላ በኩል ደግሞ የበጀት እጥረቷን አንድታስተካክል ከገንዘብ ተቋማት ጫናው በርትቶባታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *