loading
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የአፍሪካ ቀንድን የበለጠ እንደሚያስተሳስር ኬንያውያን ምሁራን ገለፁ።

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለቀጠናዊ ልማት እና ውህድት ያለው ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀዉ የዙም የገፅ ለገፅ ውይይት ነዉ ኬኒያዊዉ ሙሁር ሃሳባቸዉን የገለጹትኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ተፈጥሮኣዊ ኃብት የማንንም ፈቃድ እና ችሮታ ሳያስፈልጋቸው የማልማት መብት እንዳላቸው ምሁራኑ እንደሚገነዘቡ ገልፀው በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረሙ ስምምነቶች ተቀባይነት የሌላቸው እና ኋላ ቀር ሰነዶች መሆናቸውን ተናግረዋል። ነጻነት ያለው ማንኛውም ሀገር የሚቀበለው ስምምነት አይደለም ብለዋል።

ተወያዮቹ የቀጠናው ሕዝቦች ከአትዮጵያውያን ጋር ነን፤ ኢትዮጵያም ብቻዋን አይደለችም ብለዋል።በውይይቱ በናይሮቢ ዪኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር ፕሮፌሰር ሙሳምባይ ካቱማንጋ፣ የቀድሞ የኬንያ ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ፋራህ ማዓሊም፣ የቀድሞ የናይሮቢ ከተማ ከንቲባ እና የኢትዮጵያ-ኬንያ ወዳጅነት ማህበር ለቀ መንበር ጆ አኬች እንዲሁም የቀድሞ የኬንያ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊ እና የቀጠናዊ ውህደት እና ልማት ጉዳዮች ተንታኝ አህመድ ሃሺ ተሳትፈዋል።

ምንጭ፤- በኬኒያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *