ትራምፕ የዓለም ሙቀት መጨመር አያሳስበኝም አሉ
አርትስ 18/03/2011
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህን ያሉት የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ ሪፖርት ከቀረበላቸው በኋላ ነው፡፡
የአሜሪካ ብሄራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ጥናት ተቋም በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የተፈጥሮ አደጋ በዓለም ሙቀት መጨመር ሳቢያ መሆኑን ይፋ ቢያደርግም ትራምፕ ግን እኔን አያሳስበኝም ብለዋል፡፡
ሪፖርቱን አይቸዋለሁ የተወሰነውንም አንብቤዋለሁ ግን ከማጭበርበር የዘለለ እውነትነት የለውም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡
በሀይል ማመንጫዎች እና በተሽከርካሪዎች የሚፈጠረው የጋዝ ብክለት በዚሁ ከቀጠለ በአሜሪካ ችግሩን ለመቋቋም በየዓመቱ 155 ቢሊዮን ዶላር የሚተመን የጉልበት ወጭ ይጠይቃል፡፡
እንዲሁም የባህር ዳርቻዎችን ከብክለት ለመታደግ 118 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ኪሳራ እንደሚደርስባት ሪፖርቱ በግልፅ አስቀምጧል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ሀገራቸውን ከማስወጣታቸውም በላይ በገዛ ባለ ስልጣኖቻቸው ላይ እምነት አለማሳደራቸውም እያሰተቻቸው ነው፡፡