ቻይና በ24 ሰዓታት ውስጥ ባደረገችው ምርመራ 14 ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ አደረገች::
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣2012 ቻይና በ24 ሰዓታት ውስጥ ባደረገችው ምርመራ 14 ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ አደረገች:: ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል አስራ ሶስቱ ዋና ከተማዋ ቤጅንግ ውስጥ ሲሆኑ አንድ ሰው ደግሞ የቤጂንግ አጎራባች ከሆነችው የሄቢ ግዛት መሆኑ ታውቋል፡፡ የቻይና የጤና ኮሚሽን በሰጠው በግለጫ ሁሉም በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ከማህበረሱቡ ውስጥ ተጠርጥረው የተመረመሩ እና የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በሪፖርቱ እንዳለው ቤጂንግ ውስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በግልፅ የሚጠረጠሩና ምልክቱ ያልታየባቸው በሽተኞች አልነበሩም፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ከጁን 11 ወዲህ ከአንድ የገበያ አካባቢ ጋር በተገናኘ ንክኪ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 269 ከፍ ብሏል፡፡ ቤጂንግ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኙ እስከተበለበት እስከ ጁን 11 ደረስ ለ55 ቀናት ምንም አይነት በበሽታው የተያዙ ሰዎች አለመኖራቸውን ሪፖርት አድርጋ ነበር፡፡ ቻይና በዓለማችን ቫይረሱ መጀመሪያ የተከሰተባትና ቀድማ መከላከል የቻለች ሀገር ብትሆንም ልምዷን ለሌሎች አላካፈለችም እንዲሁም የቫይረሱን ባህርይ በወቅቱ ለዓለም አላሳወቀችም በሚል ከአሜሪካ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባቷ ይታወሳል፡፡