ቻይና ከአሜሪካ ጋር የገባችውን የንግድ ጦርነት በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
አርትስ 27/02/2011
የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዋንግ ቂሻን በንግድ ጦርነት አሸናፊ አለመኖሩን ገልፀው ቻይና ከዋሽንግተን ጋር የገባችውን የንግድጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትየሚያስችል ድርድር ለማካሄድ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ዢ በትናንትናው እለትሃገራቸው ከውጭ በምታስገባቸውሸቀጦች ላይ የምትጥለውን ቀረጥየመቀነስ እቅድ እንዳላት መናገራቸውን ተከትሎ ነው ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሀገራችን የንግድ ጦርነቱን በሰላማዊመንገድ ለመፍታት የሚያስችል ድርድርለማካሄድ ዝግጁ ናት ያሉት፡፡
ጨምረውም በአሁኑ ጊዜ አለም የሁለቱንሃገራትን ትብብር የምትፈልግበት ሰአት ነው ብለዋል፡፡
ሮይተርስ እንዳስነበበው ሁለቱ ታላላቅ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት አንዳቸው በሌላኛቸው ምርት ላይ የቀረጥ ጭማሪ በማድረግ የከፋ የንግድ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸው በአለም አቀፉ የንግድና እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው፡፡
ሮይተርስ የሃገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ እንደዘገበው ትራምፕ እና ዢ ጂንፒንግበአርጀንቲና በሚካሄደው የቡድን 20 ሃገራትስብሰባ ላይ እንደሚገናኙ እና ከስብሰባው በተጨማሪ ሃገራቱ ስላሉበት የንግድ ጦርነት ድርድር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡