loading
ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይስን ለወራት ተቆጣጥራ ከቆየች በኋላ አዲስ ታማሚዎችን ማግኘቷ ትልቅ ስጋት ፈጥሮባታል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይስን ለወራት ተቆጣጥራ ከቆየች በኋላ አዲስ ታማሚዎችን ማግኘቷ ትልቅ ስጋት ፈጥሮባታል:: ሀገሪቱ ከ100 ቀናት በላይ ዜጎቿ ከኮቪድ19 ነጻ ሆነው የከረሙ ሲሆን ሰሞኑን አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ከሶስት ቀናት ባልበለጠ ገዜ የታማሚዎቹ ቁጥር ወደ 17 ከፍ ማለቱ መሰማቱን ሲ ጂ ቲ ኤን  በዘገባው አስነብቧል፡፡ የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደርን የበሽታው ስርጭት እንደ አዲስ የተከሰተበት መንስኤ በፍጥነት እንዲጣራ አዘዋል ነው የተባለው፡፡

በተለይ በሽታው ያለባቸው ሰዎች በብዛት በተገኙባት ኦክላንድ ከተማ ጥብቅ የምርመራ ስራ እንዲከናወን ነው የሀገሪቱ መንግስት ትእዛዝ ያስተላለፈው፡፡
የኒው ዚላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ፒተርስ በሽታው እንደ አዲስ የተከሰተው ከውጭ የሚገቡ ሰዎች በሆቴሎች ራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ የሚያስገድደው ህግ በመጣሱ ሳይሆን እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡ በሽታው ከሶስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘባቸው አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *