ኖቫክ ጆኮቢች የአውስትራሊያ ኦፕን ውድድሩን በድል ጀምሯል
ኖቫክ ጆኮቢች የአውስትራሊያ ኦፕን ውድድሩን በድል ጀምሯል
15ኛ የግራንድ ስላም ክብሩን ለመቀዳጀት በማሳደድደ ላይ የሚገኘው ሰርቢያዊው የ31 ዓመት ተጫዋች ኖቫክ ጆኮቢች፤ በ2019 የአውስትራሊያ ኦፕን የመጀመሪያ ዙር ፉክክር ከአሜሪካዊው ሚሸል ክሩገር ጋር ተጫውቶ በተከታታይ ባስመዘገባቸው ዙሮች 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የዚህ የቴኒስ ጨዋታ ውጤት 300ኛ የግራንድ ስላም ድሉ ሁኖ ተመዝግቧል፡፡
የአለም ቁጥር አንዱ ጆኮቢች በሮድ ላቬር አሬናው ፉክክር አሸናፊ ለመሆን የሁለት ሰዓት ከሶስት ደቂቃ ጊዜ የወሰደበት ሲሆን በአጠቃላይ ድል ያደረገው በ6 ለ 3፣ 6 ለ 2፣ 6 ለ 2 ውጤት ነው፡፡
በቀጣዩ ሁለተኛ ዙር ከፈረንሳያዊው ዊልፍሬድ ሶንጋ ጋር የሚፋጠጥ ይሆናል፡፡