loading
አሌክሳንደር ሴፈሪን UEFAን እንዲመሩ በድጋሜ ተመረጡ

አሌክሳንደር ሴፈሪን UEFAን እንዲመሩ በድጋሜ ተመረጡ

 

አሌክሳንደር ሴፌሪን ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በድጋሜ ተመርጠዋል፡፡

የ51 ዓመቱ ሴፈሪን ሮም ላይ በተካሄደው የማህበሩ ጉባኤ በ55ቱም የማህበሩ አባላት ልዑካን ዘንድ ተፎካካሪና ተቃውሞ ሳይኖርባቸው በድጋሚ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ተሹመዋል፡፡

ስሎቬኒያዊው የህግ ባለሙያ፤ የቀድሞውን የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሚሼል ፕላቲኒ  ከኃላፊነት መነሳት ተከትሎ ነው ከሁለት ዓመት ከግማሽ  በፊት አሁን ያሉበትን ስልጣን የተረከቡት፡፡ ሚሸል ፕላቲኒ በፈፀሙት የስነ ምግባር ጥሰት ከስልጣናቸው ተሸረው በስሎቬኒያዊው አሌክሳንደር ሴፈሪን ነው የተተኩት፡፡

ፈረንሳያዊው ፕላቲኒ ከኃላፊነታቸው የተወገዱት የስነ ምግባር ጥሰት መፈፀማቸው መረጋገጡን ተከትሎ፤ በፊፋ ማዕቀብ ከተጣለባቸው በኋላ ነው፡፡

ቢቢሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *