loading
አልጄሪያ በሀገር ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት መጀመሯን ይፋ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 ክትባቱ በቻይናው ሲኖቫክ ኩባንያ የሚዘጋጅ ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ እስከ ስምንት ሚሊየን ዶዝ የማምረት አቅም አለው ተብሏል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የምርት መጠኑን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻልም የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡

የአልጀሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር አይመን ቤን አብደራሀማን የምርት ሂደቱ በጀመረበተ ወቅት በስፍራው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ይህ ለሀገራችን ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡ ገና ከዚህ የተሻለ ስኬት እናስመዘግባለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራቸውን የፋርማሲውቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ አድንቀዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አልጄሪያ ካላት 40 ሚሊዮን ህዝብ መካከል 70 በመቶ የሚሆነው ክትባት እንዲያገኝ ዘመቻ ጀምራለች፡፡

በአፍሪካ በኮቪድ-19 ከተጠቁ ሀገራት መካከል በ10ኛ ደረጃ የምትገኘው አልጄሪያ ከ203 ሺህ በላይ ዜጎቿ በበሽታው የተያዙባት ሲሆን ከነዚህ መካከል ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *