loading
አሜሪካ በኢራን ላይ በድጋሚ ማዕቀብ ለመጣል ያቀረበችዉን ጥያቄ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዉድቅ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 አሜሪካ በኢራን ላይ በድጋሚ ማዕቀብ ለመጣል ያቀረበችዉን ጥያቄ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዉድቅ አደረገ፡፡ይህንን ተከትሎም አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወሰነዉ ዉሳኔ አሸባሪዎቹን የሚደግፍ ነዉ ብላለች፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታዉ ም/ቤት አባላት አብዛኞቹ የአሜሪካን በድጋሚ ማዕቀብ መጣል መፈለግን እንደተቃወሙትና የም/ቤቱ ፕሬዚዳንት አሜሪካ አሁን ላይ በኢራን ተጨማሪ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ለመጣል የምትችልበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም ሲሉ መናገራቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተገኙት የዮ.ኤስ አምባሳደርም የትራንምፕ አስተዳደር በምንም መልኩ ቢሆን ለማድረግ ያሰበዉን ከማድረግ ወደ ኋላ የሚልና የሚፈራ አለመሆኑን እንዲሁም የምክርቤቱ አባላት ከአሸባሪዎች ጋር በጋራ መቆማቸዉ እንዳሳዘናቸዉ ገልጸዋል፡፡ከምክር ቤት አባላቱ ከተቃወሙት መካከል የሩሲያ አምባሳደር አሜሪካ ዳግም ልትጥል ያሰበችዉ ማዕቀብ ህገ ወጥ ብቻ ሳይሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋራ ያስቀመጠዉ እቅድ ጋር የማይሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ባሳለፍነዉ ሳምንት ማይክ ፖምፒዮ በ2015 የፀደቀዉን የኒዉክለር ስምምነት ኢራን በመጣስዋ ምክንያት በሀገሪቱ ላይ በድጋሚ ሁሉም ማዕቀቦች እንዲጣሉ ፍላጎት እንዳላቸዉና ምንም እንኳ አሜሪካ በ2018 ከስምምነቱ ብትወጣም በ30 ቀናት ዉስጥ በድጋሚ ልትጥል ያሰበችዉን ማዕቀብ የመጣል መብት እንዳላት መግለጻቸዉን አልጄዚራ በዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *