loading
አርሲ ዩኒቨርስቲ 300 ለሚሆኑ ስደት ተመላሾች የስራ እድል እንዳመቻቸ ገለጸ ፡፡

አርሲ ዩኒቨርስቲ 300 ለሚሆኑ ስደት ተመላሾች የስራ እድል እንዳመቻቸ ገለጸ ፡፡

ከስደት ተመላሾቹ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ሲሆን ስራ ለማስጀመርም አስፈላጊው የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮዎች ጋር በመተባበር በ11 ከተሞች በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ካሰለጠኗቸው 3500 ከስደት ተመላሽ ዜጎች 500 የሚሆኑት የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ፤ 300 ተመራቂዎችን ማቋቋም የሚያስችል ሶስት ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ እና የስራ እድል አርሲ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተመቻችቷል፡፡

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተሳሰር መስራታቸው የሚፈለገውን እድገት ለማምጣት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

አርሲ ዩኒቨርሲቲ ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ ከኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር፣ ከሲውዲን በጎ አድራጎት ድርጅት ሂውማን ብሪጅ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከስደት ተመላሽ ዜጎችን በማቋቋም ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ያከናወነውን ተግባር ሚኒስትሯ አድንቀዋል፡፡

ሚንስትሯ ሌሎች የትምህርት ተቋማት አርሲ ዩንቨርስቲ የጀመረውን ተሞክሮ በመውሰድ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመው፤ አርሲ ዩንቨርስቲን ጨምሮ ለዚህ በጎ ተግበር የተባበሩትን በሙሉ አመስግነዋል፡፡

በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው ወደ ስራ የሚሰማሩትን ከስደት ተመላሾች ሚኒስትሯ ባገኙት የስራ እድል ተጠቅመው ሠርተው በመለወጥ ለሌሎች አርዓያ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

የአርሲ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው ባሉት ሶስት ካንፓሶች ለተማሪዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያቀርቡ የሥራ እድል እንደተመቻቸላቸው ገልፀው፤ የልብስ እጥበት፣ የፀጉር ሥራ አገልግሎት፣ የፎቶ ኮፒና ፕሪንት ሥራ እንዲሁም የዳቦ አቅርቦት ስራ በድጋፍ በተገኘው ማሽኖች እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *