loading
አርሶ አደሩን በማደህየት ኢንቨስትመንቱን ማሳደግ አይቻልም አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

የክልሉ ርዕሰመስተዳድር አቶ ገዱ እንዳሉት በአማራ ክልል ለኢንቨስትመንት በሚል ሰበብ ብዙ አርሶ አደሮች መብታቸው ተጥሶ እንደነበር በመጥቀስ አርሶ አደሩን በማደህየት ኢንቨስትመንቱን ማሳደግ አይቻልም፤መሬት የሚወሰድባቸው አርሶ አደሮች ተመጣጣኝ ካሳ ማግኘት አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ቀደም ሲል በክልል የነበረውን አርሶአደሩን የማይጠቅም የካሳ ህግ የማስተካከል እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

አርሶ አደሮች እና የነባር ይዞታ ባለቤቶች መሬታቸውን ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ መደረጉ ጥያቄ በሚያነሱበት ጊዜ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ምላሽ ለመስጠት ከማገዙም በላይ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ እንዲሰራ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አቶ ገዱ አርሶ አደሮች በጉልበተኞች ጥቅማቸውን የሚያጡበት ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ካለ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ ህዝባዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ጠንክሮ መስራት እና የፍትህ ስርዓቱን ማስከበር ይጠበቅበታል ማለታቸዉን የአማራመገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *