
አርቲስት ታማኝ በየነ አዲስ አበባ ገብቷል።
ጎንደር የተወለደው ታማኝ ከ22 ዓመታት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።
አርቲስቱ ወደ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ያሄዳል፡፡በቤተ-መንግስት ከሀገሪቱ መሪዎች ጋር ይገናኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በብሄራዊ ትያትርም ቆይታ ያደርጋል፡፡
ነገ ደግሞ በሚሊንየም አዳራሽ አድናቂዎቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣህ ልዩ ዝግጅት ይኖራል ፡፡ አቀባበሉ በባህርዳርም ይቀጥላል።