loading
አሸባሪው ህወሓትን ከመቃብር ለማንሳት የሚጥሩትን መመከት ይገባል- ባልደራስ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013  ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን አሁን ላለችበት ሁኔታ የዳረጋትን ሥርዓት ከመቃብር ለማንሳት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በተባበረ ክንድ መመከት እንደሚገባ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ዶክተር በቃሉ አጥናፉ ትህነግ የአክራሪ ብሄርተኝነት የመጨረሻው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ የመንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ መልካም ቢሆንም አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን አለማቆሙ ለሠላም ቅንጣት ታህል ፍላጎት እንደሌለው ማሳያ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ዓለም አቀፉም ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን ለዚህ የዳረጋትን ሥርዓት ከመቃብር ለማስነሳት እያደረገ ያለው ጥረት ፍትሃዊነት የጎደለውና ፍጹም አድሏዊ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቡድኑ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀውን ሕግ ተላልፎ ሕጻናትን ለጦርነት ሲማግድ፣ በአፋር ክልል ሕፃናትን ሲረሽን ያሳየው ዝምታ ምን ያህል ወገንተኛና አድሏዊ በመሆኑ አበክረን እናወግዘዋለን ብለዋል፡፡ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የውጭ ጠላቶችን ጫና በመቋቋም ሽብርተኛው ህወሓትን ለማጥፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ በማንኛውም መንገድ የመሳተፍ አገራዊ ኃላፊነት እንዳለበትም ተናግረዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *