አሽራፍ ጋኒ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመበቀል ቆርጠን ተነስተናል አሉ፡፡
አሽራፍ ጋኒ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመበቀል ቆርጠን ተነስተናል አሉ፡፡
ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ይህን ያሉት አይ ኤስ አይ ኤስ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት ላይ አደጋ ማድረሱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ነው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ቡድኑ ለሰርግ በታደሙ ሰዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ60 በላይ የሚሆኑት ህይዎታቸው አልፏል፡፡
ከሟቾቹ በተጨማሪም 182 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡ ለደረሰው ጉዳትም አይ ኤስ አይ ኤስ ሃላፊነቱን ወስዷል፡፡
በዚህ ድርጊት ክፉኛ የተበሳጩት ፕሬዝዳንት ጋይን ቡድኑን የገባበት ገብተው ለመቅጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀው በዚህ እንቅስቃሴ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆምም ጠይቀዋል፡፡
በአፍጋኒስታን ጥቃቱ የደረሰው አሜሪካ ታሊባኖች እና የሀገሪቱ መንግስት እንዲስማሙ እና ጦሯን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ውይይት በጀመረችበት ወቅት ነው፡፡
ታሊባኖች ከጥቃቱ ጀርባ እንደሌሉበት በመናገር ድርጊቱን ቢያወግዙም ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ግን ማንም ከደሙ ንፁህ አይደለም ብለዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ