loading
አትሌት ሀጎስና ፎቴን በታላቁ ሩጫ አሸንፈዋል ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ የተካሄደው የቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ44 ሺ በላይ ተሳታፊዎችን አስተናግዶ ተጠናቋል
አርትስ ስፖርት 09/03/2011
መነሻና መድረሻውን ስድስት ኪሎ አድርጎ በተካሔደው የዘንድሮዉ የሩጫ ውድድር በሴቶች አትሌት ፎቴን ተስፋዬ፣ ፀሀይ ገመቹ እና ፅጌ ገብረሰላማ እንዲሁም በወንዶች ሀጎስ ገብረሂወት፣ ቦንሳ ዲዳ እና ጥላሁን ሀይሌ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል ።
አንደኛ ለወጡ አትሌቶች የመቶ ሺ ብር ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቁ አትሌቶች የዋንጫ እና የገንዝብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ። ለአሸናፊ አትሌቶ፤ የገንዘብ ሽልማቱ የሚሰጠው ከአበረታች መድሀኒት ነፃ መሆናቸው በምርመራ ሲረጋገጥ መሆኑ በአዘጋጆቹ በኩል አስቀድሞ መገለፁ ይታወሳል ።
የኤርትራ፣ ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያና፣ ቦትስዋና አትሌቶች እንዲሁም አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች አና ሌሎች በውድድሩ ተሳትፈዋል።
የአምባሳደሮች፣ የበጎ አድራጎት፣ የዊልቸር ሯጮች የተወዳዳሩ ሲሆን ሽልማታቸውን ወስደዋል ።
ዉድድሩን ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች የአረንጓዴና ቢጫ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል ።አትሌት ሀጎስና ፎቴን በታላቁ ሩጫ አሸንፈዋል
ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ የተካሄደው የቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ44 ሺ በላይ ተሳታፊዎችን አስተናግዶ   ተጠናቋል።
መነሻና መድረሻውን ስድስት ኪሎ አድርጎ በተካሔደው የዘንድሮዉ የሩጫ ውድድር በሴቶች አትሌት ፎቴን ተስፋዬ፣ ፀሀይ ገመቹ እና ፅጌ ገብረሰላማ እንዲሁም በወንዶች ሀጎስ ገብረሂወት፣ ቦንሳ ዲዳ እና ጥላሁን ሀይሌ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል ።
አንደኛ ለወጡ አትሌቶች የመቶ ሺ ብር ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቁ አትሌቶች የዋንጫ እና የገንዝብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ። ለአሸናፊ አትሌቶ፤ የገንዘብ ሽልማቱ የሚሰጠው ከአበረታች መድሀኒት ነፃ መሆናቸው በምርመራ ሲረጋገጥ መሆኑ በአዘጋጆቹ በኩል አስቀድሞ መገለፁ ይታወሳል ።
የኤርትራ፣ ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያና፣ ቦትስዋና አትሌቶች እንዲሁም አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች አና ሌሎች በውድድሩ ተሳትፈዋል።
የአምባሳደሮች፣ የበጎ አድራጎት፣ የዊልቸር ሯጮች የተወዳዳሩ ሲሆን ሽልማታቸውን ወስደዋል ።
ዉድድሩን ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች የአረንጓዴና ቢጫ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *