loading
አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

በሁለቱ ግለሰቦች መያዝ ላይ አስተያየታቸውን የተጠየቁት የቀድሞው የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እስሩ ላይ ጥርጣሬ እንዳለቸውና ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል።

የቀድሞው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸው እንዳስደነቃቸውና በዚህ ደረጃ ያልጠበቁት መሆኑን አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

ለእስሩ ሌላ ምክንያት ካለ በግልጽ እንዲነገር የጠየቁት አቶ ጌታቸው ከሙስና አንጻር የሚጠየቁ ከሆነ አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በመጨረሻው ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

“እንደ ፓርቲው ከፍተኛ አመራር እርምጃው አስደንቆኛል። ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው የሚነሳ በርካታ ሰዎች አሉ፤ መናገር የምፈልገው በረከትና ታደሰ ግን ከዚህ አንጻር በመጨረሻው ደረጃ ላይ ሊቀመጡ የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን ስለማንም በእርግጠኝነት መናገር አልችልም” ብለዋል፡፡

ለእራሳቸው ይሰጉ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው በግላቸው ምንም ስጋት እንደሌላቸው ነገር ግን በእሳቸው ላይ የተቀነባበረ ክስ ቢቀርብባቸው ብዙም እንደማይደንቃቸው ተናግረዋል።

ጨምረውም ቢሆንም አመራሩ ይህን ያህል ይወርዳል ብለው ስለማያስቡ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገሮችን ያስተካክላሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

አንድ ሰው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ወይም የክልል ወይም የፌደራል መንግሥትን የሚተች በመሆኑ ለእስር የሚዳረግ ከሆነ፤ ተገቢውን ፍትህ ያገኛል ብሎ መጠበቅ በእኔ በኩል የዋህነት ነው። ቢሆንም ተገቢውን ፍትህ ያገኛሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ትናንት አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና  በክልሉ ፍርድ ቤት ስለሚዳኙ ወደ ባህር ዳር መወሰዳቸውን የአማራ ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *