አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ ጋር ተወያዩ
አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ ጋር ተወያዩ
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በዩጋንዳ ኢንቴቤ ከተማ ከዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ጋር ተዋያይተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ኢንቴቤ ከተማ በሚገኘው ፅህፈት ቤታቸው አቶ ደመቀን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሁለቱ ከፍተኛ ባለሰልጣናት በቀጠናዊ ትብብር እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።
በተለያዩ መስኮች ለረጅም ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መግባባት ላይ ደርሰዋል።
ሁለቱ አገሮች በቀጠናው ዙሪያ በሚስተዋሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይም የተወያዩ ሲሆን በቀጣይ በቀጠናው ትብብራቸውን ለማጥጠቅ በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ተስማምተዋል።
አቶ ደመቀ በጉብኝታቸው ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ማድረሳቸዉን ከዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል