አይቤክስ ኮሌጅ ከፍለው መማር ለማይችሉ 150 ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ፣ጥር 24፣ 2013 አይቤክስ ኮሌጅ ከፍለው መማር ለማይችሉ 150 ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ኮሌጁ ከተቋቋመ ከ2002 ጀምሮ በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን ያስታወሱት የኮሌጁ ዲን አቶ ተስፍዬ አሰፋ ፤ እስካሁን ድረስ ከፍለው መማር ለማይችሉ 150 ዜጎች ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት ወደ ስራ ማስግባታቸውን ተናግረዋል።
በዘንድሮው ዓመት በሆቴል ማኔጅመንት በዲግሪ ፕሮግራም እና በቴክኒክ እና ሙያ ዘርፎች ከ350 በላይ ሰልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎቹ ውሰጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። ኮሌጁ የዘንድሮ ተመራቂዎቹን ጨምሮ 6 ሺህ ሰልጣኞችን አስተምህሮ ማስመረቁን አስታዉቋል።