አዲስ አበባ ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው
አዲስ አበባ ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው።
የቤተ-መፅሐፍት ግንባታው አራት ኪሎ ከፓርላማ ፊትለፊት ከአርበኞች ህንፃ ጎን የሚገነባ ሲሆን በ38,687 ካሬ ሜትር ላይ ያርፋል ተብሏል፡፡
በአንድ ጊዜ 3ሺህ 500 ሰው የማስተናገድ አቅም ያለውና በቀን እስከ 10,000 ሰው መቀበል የሚችለው ማዕከሉ ለህፃናት እና አዋቂዎች የሚሆን የማንበቢያ እና የአረንጓዴ ስፍራ አለው ነው የተባለው፡፡
እንደ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ገለፃ ከ100 ሰው በላይ የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት የስብሰባ አዳራሾች ያሉት ማዕከሉ ለደራሲያን ፣ ከያኒያን እና የጥበብ ሰዎች የሚሆን የመለማመጃ እና የቴአትር ማዕከላት እንዲሁም ከ130 በላይ መኪኖችን የሚያቆም ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ይኖሩታል፡፡
ይህ ለመዲናችን አዲስ አበባ ተጨማሪ ውበት የሚሰጥ እና በአይነትም ሆነ በይዘት ለሃገራችን የመጀመርያ የሆነው የአዲስ አበባ ቤተ-መፅሐፍት በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ አገልግሎት እንደሚገባም ይጠበቃል፡፡