loading
አዲስ አበባና በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች ውስጥ የሚታየው የነዳጅ እጥረት በሕገወጥ ንግድ ምክንያት የተከሰተ ነው ተባለ

አርትስ 19/03/2011

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም እንደገለጹት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህበአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በተደጋጋሚ የነዳጅ እጥረት እያጋጠመ ነው፡፡

ለእጥረቱ ዋነኛ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች  እየተቀዳ በየመንደሩ ስለሚሸጥ ነው ብለዋል፡፡

ሕገወጥ ግብይቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ በተለይ ካለፈው ወር ወዲህ እጥረቱ መባባሱን አስታውቀዋል፡፡

መንግሥት በቂ የሆነ ነዳጅ በማስመጣት በአግባቡ እያቀረበ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህእየተስፋፋ የመጣው ሕገወጥ የነዳጅ ሽያጭ አሁን እየታየ ላለው ችግር ዋነኛ ምክኒያት ነው ብለዋል፡፡

ህገ ወጥነቱን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለ ጥረት የላላ መሆኑ ደግሞ ችግሩን እንዳባባሰው ጠቁመዋል ብሏል የሪፖርተር ዘገባ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *