አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ተበረከተ::
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ተበረከተ በሶማሌ ክልል በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።
በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ የተመራ ከጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የተውጣጣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በሶማሌ ክልል በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ስድስት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ስድስት ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት የሚውል የመድሃኒት፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶችን አስረክቧል።
ድጋፍ የተደረገው መድሃኒት፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች በሁለት ዙር በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል ወደ ጤና ተቋማት የሚደርስ ርክክብ መደረጉ ተገልጿል። በቀጣይም በድርቅ ለተጎዱ የኦሮሚያ፣ ደቡብ ክልል እና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምግብና መድሃኒት አቅርቦት እንደሚቀጥል ወ/ሮ ሰሀረላ መግለጻቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡