አፍሪካ የአሮጌ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ብክለትን እያስከተለ ነዉ ተባለ፡፡
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 በአፍሪካ የአሮጌ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ብክለትን እያስከተለ ነዉ ተባለ፡፡ ቢቢሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ሪፖርትን ጠቅሶ እንደዘገበዉ፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሮገ የሚገፉ ተሽከርካሪዎች ከሀብታም ሀገራት እየወጡ በድሃዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ማራገፊያ ሆነዋል ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ አፍሪካን የቆሻሻና የብክለት ማዕከል ማድረጉን ሪፖርቱ ገልጿል፡፡ ከ2015 አስከ 2018 እ.ኤ አ ባሉት ግዚያት 14 ሚሊዮን አሮጌ ተሸከርካሪዎች ዉስጥ ግማሽ ያህሉ ከተለያዩ የአዉሮፓሀገራት፤ ከጃፓንና አሜሪካ ወደ አፍሪካ ተልከዋል፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለሞያዎች ወደ አፍሪካ ሀገራት ከሚላኩ ተሸከርካሪዎች ዉስጥ 80 በመቶ ያህሉ የደህንነት መጠበቂያዎቻቸዉ የማይሰሩና የአየር በካይ የሆኑ ናቸዉ ብለዋል፡፡ከአየር ንብረት በተጨማሪም አደጋ ለማድረስ ቅርብ የሆኑ እነደሆኑ ተገልጿል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም እንዳወጣዉ ሪፖርት አሮጌ ተሸከርካሪዎችንም አስመጪዎችም ሆኑ ተቀባዮች በጋራ አህጉሪቷን ለአየር ብክለት እየዳረጓት እንደሆነ ገልጿል፡፡ከአፍሪካ ቀጥሌ በአሮጌ ተሸከርካሪዎች ማራገፊያ በመሆን ለብክለት የተጋለጡት የእስያ እና የላቲን አሜሪካ ሀገራት ናቸዉ ተብሏል፡፡