loading
ኢስፔራንስ የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆን ቻለ

አርትስ ስፖርት 01/03/2011

የ2018 ቶታል ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ 22ኛ ውድድር ትናንት ምሽት ቱኒዚያ ላይ በተደረገ የደርሶ መልስ የፍፃሜ ጨዋታ ተጠናቋል፡፡ በመጀመሪያው የአሌክሳንድሪያው ግጥሚያ አል አህሊ ኢስፔራንስን 3 ለ 1 በመርታቱ የዋንጫው አሸናፊ ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም ኢስፔራንስ በሜዳው በስታዴ ኦሎምፒክ ዴ ራዴስ 3 ለ 0 በማሸነፍ አስገራሚ ድል አስመዝግቧል፡፡ በቡድኑ ብዙ የመሰለፍ ዕድል የማይሰጠው አማካዩ ሳአድ በጉር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አጥቂው አኒስ ባድሪ ሌላኛዋን ግብ ጨምሯል፡፡ ኢስፔራንስ ዴ ቱኒስ በአጠቃላይ ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ ዋንጫውን ለሶስተኛ ጊዜ ማንሳት ችሏል፤ የቡድኑ አጥቂ አኒስ ባድሪ በ8 ጎሎች የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ መሆን ችሏል፡፡ በፍፃሜው ግጥሚያ የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ እና የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በክብር እንግድነት የታደሙ ሲሆን ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በብቃት መርተውታል፡፡፡ ኢስፔራንስ የውድድሩ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ የዋንጫና የ2.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አሸናፊ መሆን ችሏል፤ በሚቀጥለው ወር በዩናይትድ አረብ ኢምሬቶች በሚካሄደው የ2018 የፊፋ የዓለም ክለቦች ውድድር ደግሞ ተካፋይ ይሆናል፡፡ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ አል አህሊ 8 ጊዜ ሻምፒን በመሆን ባለድል ሲሆን ቲፒ ማዜንቤና ዛማሊክ አምስት ጊዜ ማንሳት ችለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *