ኢትዮጵያ በዓመት 50 ሚሊየን የአንስሳት ክትባት ማምረት የሚያስችል መሳሪያ በእርዳታ አገኘች
አርትስ 13/02/2011
አለም አቀፉ የምግብና ግብርና ተቋም /ፋኦ/ እና የአውሮፓ ህብረት ለብሔራዊ የእንስሳትህክምና ተቋም የክትባት ማምረቻ መሳሪያአበርክተዋል።
መሳሪያው ተቋሙ በበጎችና ፍየሎችየሚከሰቱ የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከልየሚያስችል 50 ሚሊዮን ቴርሞ ቶሌራክትባት በየአመቱ የሚያመርት ሲሆን፤በፍየሎችና በጎች የሚከሰቱ በሽታዎችንለመከላከል የሚደረገውን ጥረትእንደሚያግዝና የቤት እንስሳት የምግብዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚያስችልተነግሯል።
በርክክቡ ወቅት የብሄራዊ እንስሳት ህክምናተቋም ጀነራል ዳይሬክተር ዶክተር ማርታያሚ፥ የመሳሪያ ድጋፉ በፍየልና በጎችየሚከሰተውን በሽታ ለመቆጣጠርለሚደረገው ጥረት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ተቋሙ የመሳሪያ ድጋፍ ከማድረጉ በፊት 11 ሚሊየን የክትባት መድሃኒቶችን በመላሀገሪቱ አሰራጭቶ ነበር፡፡