loading
ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት ቀዉስ የለዉጡ የአያያዝ ችግርና የኦነግ ግልፅ ባልሆነ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ነዉ ሲሉ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት ቀዉስ የለዉጡ የአያያዝ ችግርና የኦነግ ግልፅ ባልሆነ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ነዉ ሲሉ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ገለፁ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ይህን ያሉት በአርትስ ቴሌቪዥን የፓርቲዎች የምርጫ ክርክር ፕሮግራም ላይ ህብር ኢትዮጵያን በመወከል ቀርበዉ ባደረጉት የምርቻ ክርክር ላይ ነዉ፡፡

የህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ ተወካዩ ኢ/ር ይልቃል በኢትዮጵያ አሁን እየታየ የሚገኘዉ የእርስ በእርስ ግጭትና አለመራጋጋቶች እንዲፈጠሩ ዋነኛዉ ምክኒያት የለዉጡ ሃይል ግልፅ ያለመሆንና ለዉጡን የያዘበት መንገድ ችግር በመፍጠሩ ምክኒያት መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

ኢ/ር ይልቃል፣ አክለዉም በለዉጡ ማግስት ኦነግና የታጠቁ ሃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በመንግስት እና በታጠቁት ሃይሎች መካከል የነበረዉ ስምምነት ግልፅ ባለመሆኑ ምክኒያት ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ አዳጋች ሆኗል በማለት ተናግረዋል፡፡ ህብር ኢትዮጵያ ቢመረጥ ይላሉ ኢ/ር ይልቃል፣ የታጠቁ ሃይሎች የህዝብ ጥያቄ ካላቸዉ በመደራደር ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጣ ይደረጋል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *