ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አደነቁ፡፡ ፕሬዝዳንቱ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አደነቁ፡፡ ፕሬዝዳንቱ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ለኢትዮጵያ ያላቸዉን አድናቆትና አጋርነት የገለጹት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በነበራቸዉ ዉይይት ወቅት ነዉ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ከልኡካቸዉ ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በነበራቸዉ ቆይታ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ያደነቁ ሲሆን ፤ ፕሬዚዳንቱ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ትብብር እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል:: የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ወሳኝ የፋይናንስና ዕውቀት ምንጭም ነው ብለዋል::
ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እንዳገኘነዉ መረጃ በሚያዝያ ወር አጋማሽ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዴቪድ ማልፓስ ሦስት የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ::