loading
ኢትዮጵያ ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን ልታከብር ነው
አርትስ 13/03/2011
“ጤናማ የአኗኗር ዜይቤ ለጤናማ ሕይወት” በሚል መሪ ቃል መንገዶችን ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ በማድረግ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማክበር ማቀዱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችንና አጋላጭ መንስኤዎቻቸውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በማሰብ መርሃ ግብሩ እንዳዘጋጀ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ፕሮግራሙ ለጊዜው በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በሂደት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ከተሽከርካሪ ነፃ በሚሆኑ የተመረጡ መንገዶች ላይ የአካል እንቅስቃሴዎች፣ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ነፃ ምርመራዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ይከናወናሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *