loading
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የሃቢታት ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የሃቢታት ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

ከየተባበሩት መንግስታት ድርጅት   አጠቃላይ የማሻሻያ ሂደት ውጤት የሆነውና በናይሮቢ  የተጀመረው የ1ኛው የተባበሩት መንግስታት ድጅት   የሃቢታት ጉባኤ ኢትዮጵያን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል አድርጎ መርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኪንያ ገልጿል።

ኢትዮጵያ የስራ አስፈፃሚውን ቦርድ ለአራት አመታት እ.ኤ.አ ከ2019 – 2022 ድረስ ታገለግላለች።
ኢትዮጵያ የአፍሪካን አቋም በመደገፍና በማራመድ በኩል ያላትን የፀና አቋም ለአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ እንደሆነ አገራችንን ለቦታው በማጨት መግለፃቸው አገራችን በአፍሪካውያን ዘንድ ያላት የላቀ ተቀባይነት መቀጠሉን ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ኢትዮጵያም ለዚህ ምስጋናዋን በስራ አስፈፃሚ ቦርዱ ላይ የአፍሪካን አቋም በማንፀባረቅ ገልፃለች።
በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ፣ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ፣  የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን መሪ ስም፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አለን መልዕክቱን አስተላልፏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *