ኤርትራ ልክ እንደ ጎረቤቷ ኢትዮጵያ ዜጎቿን ወደ ቤታችሁ ተመለሱ እያለች ነው፡፡
ኒውስ አፍሪካ እንደዘገበው የኤርትራው የውጨ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳልህ ከዶቸዌሌ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኤርትራዊያን ወደ ሀገራቸው ገብተው መኖር ይችላሉ ብለዋል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እንዳሉት በየትኛውም ምክንያት ከሀገሩ የወጣ ማንኛውም ኤርትራዊ ዜጋ ከእንግዲህ በፈለገው ጊዜ ወደ ሀገሩ ተመልሶ የመኖርና የመስራት ነጻነቱን የሚጋፋው አካል የለም፡፡
ከኢትዮጵያ ጋር ለዓመታት ሰላምም ጦርነትም የለም ስትባባል የቆየችው ኤርትራ በቅርቡ ከኢትዮጵያና ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ጋር ሰላማዊ ግንኙነቶችን መጀመሯ ይታወሳል፡፡
አሁን ደግሞ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎቿን በሰላም ወደ እናት ሀገራችሁ ግቡ የሚል መልእክት አስተላልፋለች፡፡
አርትስ 24/12/2010