loading
ኤርትራ የፕሬስ ነጻነትን እንድትፈቅድ ከመብት ተሟጋቾች ጥሪ ቀረበላት

አርትስ 10/1/2011
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ ክንፍ ኤርትራ በሀገሪቱ የነበሩትን የግል ሚዲያዎች የዘጋችበትን 17ኛ ዓመት ባሰበበት ወቅት ነው ይህን ጥሪ ለአስመራ ያቀረበው፡፡
የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) በበኩሉ በኤርትራ ያለው ለጋዜጠኞች ያልተመቸ ሁኔታ እንዲስተካከል እንዲሁም በእስር የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡
በተለያየ ጊዜ የሚወጡ ሪፖርቶች በርካታ ጋዜጠኞች ኤርትራ ውስጥ እንግልት ሲደርስባቸው እንደነበር አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *