እስራኤል በድብቅ መሳሪያ ሲያጓጉዝ አገኘሁት ያለችውን ፈረንሳዊ በእስር ቀጣች፡፡
እስራኤል በድብቅ መሳሪያ ሲያጓጉዝ አገኘሁት ያለችውን ፈረንሳዊ በእስር ቀጣች፡፡
ሮሜይን ፍራንክ የተባለው ፈረንሳዊ ከጋዛ ወደ ዌስት ባንክ በድብቅ የጦር መሳሪያዎችን ሲያሸጋግር እንደተደረሰበት ፍርድ ቤት ቀርቦ በማመኑ በ7 ዓመት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡
ታይምስ ኦፍ እስራኤል እንደዘገበው ፍራንክ የእስር ቅጣቱ ቀላል የሆነለት መሳሪያውን ለፍልስጤማዊያን ሊያጓጉዝላቸው የተስማማው ንንዘብ ለማግኘት ሲል ብቻ መሆኑ ስለተረጋገጠ ነው፡፡
ተከሳሹ በሀገሩ ፈረንሳይ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሾፌር ሆኖ ሲያገለግል የዲፕሎማቲክ ተሽከርካሪ በመጠቀም 70 ሽጉጦችን እና 2 አውቶማቲክ ጠብመንጃዎችን ገንዘብ ተከፍሎት ሲያገጓጉዝ ነው በእስራኤል የፀጥታ ሰዎች የተያዘው፡፡
የእሰራኤል አቃቤ ህግ ባሰባሰበው ማስረጃ ፍራንክ መሳሪያዎቹን ለፍልስጤማዊያን በማጓጓዝ 7 ሺህ 600 ዶላር እንደተከፈለው ደርሶበታል፡፡
ተከሳሹ በተጨማሪ 8 ሺህ 300 ዶላር የገንዘብ ቅጣት እና ሌላ የ18 ወር የገደብ የእስር ቅጣትም ተወስኖበታል፡፡
መንገሻ ዓለሙ