loading
ኦታራ ፍትህ ረሷን ትግለጥ እያሉ ነው፡፡

ኦታራ ፍትህ ረሷን ትግለጥ እያሉ ነው፡፡

የአይቮሪኮስቱ ፕሬዝዳንት አላሳኒ ኦታራ የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሎረን ባግቦን ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በነፃ ማሰናቱን ተከትሎ ነው ይህን ያሉት፡፡

ኦታራ እና ባግቦ በስልጣን ግብግብ ውስጥ በነበሩበት ወቅት በተፈጠረው ግጭት ከ30 ሺህ በላይ አይቮሪኮስታዊያን ህይዎታቸው አልፏል፡፡

ለዚህ ሁሉ ግድያ መንስኤው ስልጣን በሰላም አልለቅም ብለው ወደ ፀብ የገቡት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሎረን ባግቦ ናቸው ብሎ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ቆርጦባቸው ነበር፡፡

ይሁን እና ከዓመታት ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ ባግቦን እና አጋሮቻቸውን ጥፋት አላገኘሁባቸውም በማለት በነፃ አሰናብቷቸዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ኦታራ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተገኝተው ባደረጉት የጎንዮሽ ስብሰባ ለ30 ሺህ ሰዎች ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል መኖር አለበት ብለዋል፡፡

የባግቦንን መፈታት መቃወማቸው በፍርድ ቤቱ ስራ ጣልቃ መግባት ነው ለሚሉ ወገኖች “እኛ በሌሎች ስራ ጣልቃ እየገባን ሳይሆን  ፍትህ  ራሷን ትገልጥ ዘንድ እየተከራከርን ነው” ብለዋል ፕሬዝዳንት ኦታራ፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *