ከመቶ ሺህ በላይ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል ሊፈጠርላቸው ነው ተባለ
ከመቶ ሺህ በላይ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል ሊፈጠርላቸው ነው ተባለ
አርትስ 20/02/2011
የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሀገሪቱ ያላትን የውሀ ሀብት በመጠቀም በመስኖ ልማቱ ላይ ወጣቶች እንዲሰማሩ እቅድ ይዞ እየሰራ ነው።
ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እንደተናገሩት አንድ መቶ ሺህ ወጣቶች በመስኖ ልማት የስራ እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ።
የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ በበኩላቸው፥ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የወጡ እና በስራ ላይ የማይገኙ ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራውቅድሚያ ያገኛሉ ብለዋል።
የስራ ዕድል ፈጠራው በብዛት በግብርናው ዘርፍ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተመራቂዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፥ ወጣቶቹ በኢንተርፕራይዝ ወደስራ ይገባሉ ብለዋል።
በዚህ መሰረትም በበጀት ዓመቱ እስከ አንድ ሺህ ኢንተርፕራይዞችን ተደራጅተው ወደስራ ይገባሉ እንደዳይሬክተሩ ገለጻ።
የስራ ዕድሉ የመስኖ ፕሮጀክት ባለባቸው ክልሎች የተዘጋጀ ሲሆን፥ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ አማራ፣ ደቡብ እና ትግራይ ክልሎች ፕሮግራሙ ይተገበርባቸዋል ተብሏል። ዘገባው የፋና ነው።