ከሰባት ሚሊዮን በላይ የየመን ህጻናት ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ
ከሰባት ሚሊዮን በላይ የየመን ህጻናት ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ
አርትስ 22/02/2011
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በየመን ያለው ጦርነት ማብቃቱ ብቻውን የህጻናቱን ህይወት ማዳን አይችልም።
በአሁኑ ወቅት ከአምስት አመት በታች ያሉ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን የየመን ህጻናት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን 4 መቶ ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለከባድ የመቀንጨር በሽታ ተጠቂ ሆነዋል ብሏል የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ።
“ጦርነትን ማቆም በቂ አይደለም። የምንፈልገው ጦርነቱን አቁሞ ህዝብንና ህጻናትን ማዕከል ያደረገ የመንግስት ተግባር ሲከናወን ማየት ነው” ብሏል ዩኒሴፍ። ዘገባው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ነው።