ካርማን አልጋ ወራሾቹን ህግ ፊት እንገትራቸዋለን አሉ፡፡
የመናዊቷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሎሬት ታዋኮል ካርማን የሳውዲውን እና የአቡዳቢውን ልኡል አልጋ ወራሾች ሞሀመድ ቢን ሳልማን እና ሞሀመድ ቢን ዛይድን በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፊት እንፋረዳቸዋል ብለዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የተባበሩት መንግስታት ድርጂት በየመን የሚካሄደው የርስበርስ ጦርነት በጦር ወንጀለኝነት የሚያስጠይቅ መሆኑን በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
ካርማን እንዳሉት የመን ውስጥ ጦርነቱን የሚመሩት ብቻ ሳይሆኑ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ግጭቱ እዲባባስ የሰሩት ሁሉ ተጠያቂወች ናቸው፡፡