loading
ዜጎች ቢያንስ ትንሹን የጥራት ደረጃ ያሟሉ ቤቶች ያስፈልጓቸዋል-ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20፣ 2013 ዜጎች ቢያንስ ትንሹን የጥራት ደረጃ ያሟሉ ቤቶች ያስፈልጓቸዋል-ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

የግል ባለሀብቶች በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አሳሰቡ

በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ያለመው ሠላም የመኖሪያ ቤት ብድር ባንክ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ይፋ ሆኗል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ኢትያጵያውያን ቢያንስ ትንሹን የጥራት ደረጃ ያሟሉ የመኖሪያ ቤቶች ያስፈልጓቸዋል፡፡

በየወቅቱ እየናረ የሚሄደው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መካከለኛ የሚባል ገቢ ላላቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ፈተና መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በመኖሪያ ቤት ግንባታ ላይ የሚሰማሩ እንደ ሠላም ባንክ ዓይነት በርካታ ተቋማት ያስፈልጋሉ ማለታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በሚቀጥሉት አምስት አመታት 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ያቀደው ሠላም ባንክ በዝቅተኛ እና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን ማዕከል እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *