loading
ዞኖችና 44 ተጨማሪ ወረዳዎች የተካተቱበት አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ረቂቅ አዋጅ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀረቦ ዉይይት እየተደረገበት ነዉ

አርትስ 23/02/2011

 

ረቂቅ አዋጁ የደቡብ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 8ተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው  የቀረበው።

አዲሱ ረቂቅ አወቃቀር የመንግስት አገልግሎትን ለወረዳ ማዕከላት ቅርብ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑ ታምኖበታል።

በአዲሱ የአስተዳደር እርከን መሠረት፣ ካሁን በፊት ልዩ ወረዳ የነበረው ሀላባ ወደ ዞንነት ሲያድግ ዌራ ዙሪያ፣ ድጆ ዌራና ድጆ የተባሉ ወረዳዎች እና ቁልቶከተማ አስተዳደር ይኖሩታል።

ጋሞ ጎፋ ዞን ለሁለት ተከፍሎ ጋሞ እና ጎፋ ዞኖች እንዲዋቀር በረቂቅ አዋጁ ላይ ቀርቧል።

በረቂቅ አዋጁ መሰረት ጎፋ ዞን በስሩ ስምንት ወረዳዎች የሚኖሩት ሲሆን፥ ወረዳዎቹም ዲምባ ጎፋ፣ ገዜ ጎፋ፣ ዛላ፣ ኡባ ደብረ ፀሐይ፣ ኦይዳ፣ ሳውላ ከተማ፣መለኮዛና ጋዳ ወረዳዎች እና ቡልቂ ከተማ በዞኑ አስተዳደር ተዋቅረዋል።

ለብቻው እንደ አዲስ የሚዋቀረው ጋሞ ዞን ደግሞ 13 ወረዳዎች የሚኖሩት ሲሆን፥ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባ ምንጭ ከተማ፣ ደራማሎ፣ ቁጫ፣ ዲታ፣ካምባ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጨንቻ፣ ቦንኬ፣ ሰሜን ቦንኬ፣ ጋርዳ ማርታ፣ ቦረዳ እና ምዕራብ ቁጫ የተባሉ ወረዳዎችን ያቀፈ ይሆናል።

በረቂቅ አዋጁ ከሰገን ሕዝቦች ዞን ወጥቶ በዞንነት እንዲደራጅ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበበት ኮንሶ ዞን ደግሞ፣ በስሩ ካራት ከተማ አስተዳደር፣ ካራት ዙሪያ፣ ሰገንዙሪያና ከና የሚሉ የወረዳ መዋቅሮች ተካተዋል።

በክልሉ ነባር ዞን አስተዳደሮች ተጨማሪ አዲስ የወረዳ አስተዳደር እርከኖች እንዲቋቋሙ በረቂቅ አዋጁ ላይ ቀርቧል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በዛሬው ውሎውም በረቂቅ አዋጁ  ላይ ዉሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *